ዮሐንስ 6:69 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛስ አምነናል፤ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አንተ እንደ ሆንክም ዐውቀናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደ ሆንህ አምነናል፤ ዐውቀናልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም፤” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ እንደ ሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት። |
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ።”
ታዲያ፥ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስለ አለ ስለምን ‘በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ትናገራለህ’ ትሉታላችሁ?
እንዲሁም የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ በእምነት ወደሚገኘው አንድነት ደርሰን፥ ክርስቶስ ፍጹምና ሙሉ እንደሆነው ዐይነት እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።