ኢዮብ 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሳያግዘው ሰማይን የዘረጋ እርሱ ነው፤ እርሱ በባሕር ሞገድ ላይ ይራመዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቷል፤ በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በምድር ላይ እንደሚሄድ በማዕበል ላይ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል። |
እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦
በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።