ትንፋሽ እስካገኝ እንኳ ፋታ አይሰጠኝም፤ ሕይወቴን በሥቃይ ሞልቶታል።
ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣ ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል።
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገርን አጥግቦኛል።
የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? በዚህች አጭር ዘመን ጥቂት እንድደሰት እባክህ ተወኝ!
“በእኔ ላይ የጻፍከው ክስ እጅግ መራራ ነው፤ በልጅነቴ የሠራሁትን በደል እንኳ አልተውክልኝም፤
“ትክክለኛ ፍርድ በመከልከል፥ ሕይወቴን እጅግ መራራ ባደረገው ሁሉን በሚችል በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።
“በጭንቀት ላይ ላሉ ብርሃን፥ ኑሮአቸው በመራራ ሐዘን ለተመላ ሕይወት የሚሰጣቸው ለምንድነው?
ምራቄን እስክውጥ እንኳ ለጥቂት ጊዜም አትተወኝምን?
ወደማልመለስበት ወደ ሞት ሳልሄድ ጥቂት ደስታ እንዳገኝ እባክህ ታገሠኝ።
ቊጣህ እጅግ ከብዶኛል፤ የቊጣህም ማዕበል አጥለቅልቆኛል።
ይህን በማድረግ ፈንታ እልኸኞች ሆኑ፤ አባቶቻቸው ባስተማሩአቸውም መሠረት ለባዓል ምስሎች ሰገዱ።
ከችግር የተነሣ ሕይወት እንዲመረኝ አደረገ፤ በእሬትም አጠገበኝ።
ቀኑን ሙሉ እኔን ብቻ መላልሶ ቀጣኝ።
ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስደስት አይመስልም፤ በኋላ ግን ለተለማመዱት ሰዎች ሰላም የሞላበትን የጽድቅ ፍሬ ያስገኝላቸዋል።
እርስዋም እንዲህ አለች፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ ስላደረገው ‘ማራ’ በሉኝ እንጂ ‘ናዖሚ’ ብላችሁ አትጥሩኝ፤