እግዚአብሔር ሰይጣንን “አገልጋዬን ኢዮብን ልብ ብለህ አየኸውን? እርሱን የመሰለ ታማኝና ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም፤ እርሱ ከክፋት ሁሉ ርቆ እኔን የሚፈራ ቀጥተኛ ሰው ነው” አለ።
ኢዮብ 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥተኛና ንጹሕ ከሆንክ፥ እርሱ ፈጥኖ ወደ ተገቢ ቦታህ ይመልስሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፥ ልመናህን ፈጥኖ ይሰማሃል፥ የጽድቅህንም ብድራት ፈጽሞ ይሰጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት አሁን ስለ አንተ ይነቃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያከናውንልሃል። |
እግዚአብሔር ሰይጣንን “አገልጋዬን ኢዮብን ልብ ብለህ አየኸውን? እርሱን የመሰለ ታማኝና ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም፤ እርሱ ከክፋት ሁሉ ርቆ እኔን የሚፈራ ቀጥተኛ ሰው ነው” አለ።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።