ኢዮብ 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አረም በፀሐይ አቈጥቊጦ በአትክልት ቦታው እንደሚበዛ ክፉ ሰዎችም እንደዚሁ ይበዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይም ትኩሳት በፊት እርጥብ ነው፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፀሐይ በታች ይሻግታል፤ ጫፉም በአትክልት ቦታ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም ሳይተኵስ ይለመልማል፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል። |
አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ።