ከዚህም ሁሉ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማያትን፥ የሰማያትንም ሰማያት ከነሠራዊታቸው፥ ምድርንና በእርስዋም ላይ የሚገኘውን ሁሉ፥ ባሕሮችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ፥ ፈጠርክ፤ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ይሰግዱልሃል።
ኢዮብ 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን የምትከታተል ሆይ፤ ኀጢአት ብሠራ፣ አንተን ምን አደርግሃለሁ? ለምን ዒላማህ አደረግኸኝ? ለምንስ ሸክም ሆንሁብህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ? ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ? ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ? ስለ ምን እኔን ለአንተ ዓላማ አደረግኸኝ? ስለ ምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ? |
ከዚህም ሁሉ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማያትን፥ የሰማያትንም ሰማያት ከነሠራዊታቸው፥ ምድርንና በእርስዋም ላይ የሚገኘውን ሁሉ፥ ባሕሮችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ፥ ፈጠርክ፤ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ይሰግዱልሃል።
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።