እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
ኢዮብ 7:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ዝም አልልም! ከመንፈስ ጭንቀቴ የተነሣ እናገራለሁ፤ ከነፍሴ ምሬት የተነሣ አጒረመርማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤ በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤ በነፍሴም ምሬት አጕረመርማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እኔ አፌን አልከለክልም፤ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፤ የነፍሴንም ምሬት በኀዘን እገልጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጕራለሁ። |
እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፥ በብዙ እንባም ሆኜ የጻፍኩላችሁ በጣም የምወዳችሁ መሆኔን እንድታውቁ ብዬ ነው እንጂ ላሳዝናችሁ ብዬ አይደለም።