ለዚህ ዐይነቱ ምግብ ፍላጎት የለኝም፤ ብበላውም እንኳ ጤና ይነሣኛል።
እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤ ለመንካትም አልፈልግም።
ሰውነቴ ትነካው ዘንድ እንቢ አለችው፥ እንደሚያስጸይፍ መብል ሆነብኝ።
ሰውነቴ ማረፍ አልቻለችም፤ የሥጋዬን ክርፋት እንደ አንበሳ ክርፋት እመለከተዋለሁና።
እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ወደ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ያለችኝን ትንሽ ዱቄት ለልጄና ለእኔ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያም በኋላ በራብ ከመሞት አንተርፍም።”
እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
በምግብ ፈንታ እቃትታለሁ፤ ጩኸቴም እንደ ፈሳሽ ውሃ ነው።
በዚህ ዐይነት ሕመምተኛው እህል መቅመስን ያስጠላዋል፤ ምርጥ የሆነ ምግብ እንኳ አያስደስተውም።
ጨው ያልገባበት ጣዕም ያጣ ምግብ ይበላልን? የእንቊላልስ ውሃ ይጣፍጣልን?
“ምነው እግዚአብሔር የምመኘውን በሰጠኝ! ምነው ጸሎቴንስ በሰማኝ!
ምግቤ ዐመድ ሆኖአል፤ እንባዬም ከምጠጣው ነገር ጋር ተደባልቆአል፤
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለኢየሩሳሌም የሚቀርበው ምግብ ሁሉ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝብ በፍርሃትና በስጋት ተሞልተው የሚበሉትን እህልና የሚጠጡትን ውሃ እየመጠኑ እንዲመገቡና እንዲጠጡ አደርጋለሁ።
ሥጋም ሆነ ሌላ ጥሩ ምግብ አልተመገብኩም፤ የወይን ጠጅም ፈጽሞ አልቀመስኩም፤ ሦስቱ ሳምንቶች እስኪያልፉ ድረስ ራሴን ቅባት አልተቀባሁም።