ኢዮብ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በታየ ኖሮ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምነው ሐዘኔ በተመዘነ! መከራዬም ሚዛን ላይ በተቀመጠ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ትካዜዬ ምነው በተመዘነ! መከራዬም በሚዛን ላይ ምነው በተቀመጠ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእናንተ አንዱ መቅሠፍቴን ምነው በመዘነ ኖሮ! መከራዬንም በአንድነት ምነው በሚዛን ላይ ባኖረው ኖሮ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ! |