ኢዮብ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግር ከዐፈር አይነሣም፤ መከራም ከመሬት አይበቅልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ችግር ከምድር አይፈልቅም፤ መከራም ከመሬት አይበቅልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችግር ከትቢያ አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይበቅልም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግር ከምድር አይወጣምና፥ መከራም ከተራሮች አይበቅልምና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ችግር ከትቢያ አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይበቅልም፥ |
በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል።
ሳይዘራ ገቦ ሆኖ የበቀለውንም እህል አትሰበስብም፤ ካልተገረዘውም የወይን ሐረግ ፍሬውን አትሰበስብም፤ ያ ዓመት ምድሪቱ ፍጹም ዕረፍት የምታደርግበት ጊዜ ነው።
ለጦርነት የሚያዘጋጅ መለከት በከተማ ውስጥ ሲነፋ በፍርሃት የማይንቀጠቀጥ ሕዝብ ይኖራልን? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይመጣልን?
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።
ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”