ኢዮብ 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባል፤ እርሻዎችንም በውሃ ያረሰርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ ከሰማይም በታች ውኃን ይልካል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል። |
በእርሱ ትእዛዝ ከሰማይ በላይ ያሉ ውሃዎች የመናወጥ ድምፅ ያሰማሉ፤ እርሱ ደመናዎችን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ነፋስንም ከማከማቻው ይልካል።
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።
አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።
ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”