ዓሣ ነጋዴዎች እርሱን ለመግዛት ይጫረታሉን? ቈራርጠውስ ይከፋፈሉታልን?
ነጋዴዎችስ በርሱ ላይ ይከራከራሉን? ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?
የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው? በጥርሶቹ ዙሪያ ግርማ አለ።
አንጀቶቹ የናስ አራዊት ናቸው፤ የቆዳውም ጽናት እንደ ዓለት ድንጋይ ነው።
እንደ ወፍ እርሱን ልታለማምድ ትችላለህን? ወይስ ሴቶች ልጆችህን እንዲያጫውት አስረህ ታኖረዋለህን?
ቆዳውን በፈለግህበት ቦታ በጦር መብሳት፥ ጭንቅላቱንም በሾተል ወግተህ መሰንጠቅ ትችላለህን?
ፍልስጥኤማውያን እርሱን ባዩት ጊዜ ከእርሱ ጋር እንዲቈዩ ሠላሳ ወንዶች ወጣቶችን መርጠው ላኩለት።