ኢዮብ 41:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ ታላላቅ የሆኑትን ፍጡሮች እንኳ ይንቃል፤ እርሱ በአራዊት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፍ ያሉትን ሁሉ በንቀት ይመለከታል፤ በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።” |
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ላለችው የሰማርያ ከተማ ወዮላት! መሪዎችዋ በመጠጥ የተሞሉ ሰካራሞች ናቸው ነገር ግን እነርሱ ደርቆ እንደሚረግፍ አበባ ይሆናሉ።
ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።
ያየሁት አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፥ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው።