ኢዮብ 41:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ የሚያስፈሩ ጥርሶች ያሉበት አፉን ከፍቶ መንጋጋውን ሊያላቅቀው የሚችል ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን፣ የአፉን ደጅ ማን ደፍሮ ይከፍታል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንገቱ በጣም ጠንካራ ነው፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአካሉ ሥጋም የተነባበረ ነው፤ ጎጂ ነገርን ቢያፈስሱበትም አይንቀሳቀስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንገቱ ኃይል ታድራለች፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል። |
“ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።