ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?
ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው? ከሰማይ በታች ማንም የለም።
ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት ግልጥልጥ ያለ ነው፤ ምንም ነገር ሊሸፍነው አይችልም።
እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
ታዲያ፥ አንተ ንስሓ መግባት እንቢ እያልክ፥ አንተ በምታቀርበው ሐሳብ መሠረት እግዚአብሔር ምኞትህን እንዲፈጽምልህ ትፈልጋለህን?
ጻድቅ ብትሆን ለእግዚአብሔር ምን ትሰጠዋለህ? እርሱ ከአንተ ምንም አይፈልግም።
“ስለ ሌዋታን እግሮች፥ ስለ ብርቱ ኀይሉ ስለሚያምረው አካሉ ሳልገልጥ አላልፍም።
ሳይታሰብ በድንገት ተራራዎችን ያናውጣል፤ በቊጣውም ይገለባብጣቸዋል።
ሰማይ የእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጥቶአል።
በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።
ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።
“ዓለምና በውስጥዋ ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ስለ ሆነ የምራብ ብሆን እንኳ ለአንተ አልነግርህም ነበር።
አሁንም እነሆ፥ ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆን የተለያችሁ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤
ለእግዚአብሔር የሚያበድርና ያበደረውንም የሚወስድ ማነው?”
“ምድርና በእርስዋም ያለው ሁሉ የጌታ ነው።”
ነገር ግን አንድ ሰው “ይህ ሥጋ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ።
ሰማይና ከሰማይ በላይ ያሉ ሰማያት፥ ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ማናቸውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።
የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ቀድሞ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ይሸጋገራል።