አንተ ታላቅና ኀያል ነህ፤ በክብር፥ በውበትና በግርማም የተሞላህ ነህ፤ በሰማይና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአንተ ነው፤ አንተ ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክና በሁሉም ላይ ሥልጣን ያለህ ንጉሥ ነህ፤
ኢዮብ 40:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ከሆነ ራስህን በግርማ ሞገስ ተቀዳጅ ክብርንና ገናናነትንም ተጐናጸፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግርማንና ልዕልናን ተላበስ እንጂ፥ ሞገስንና ክብርን ተጐናጸፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪ ልዕልናንና ኀይልን ተላበስ፤ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፥ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። |
አንተ ታላቅና ኀያል ነህ፤ በክብር፥ በውበትና በግርማም የተሞላህ ነህ፤ በሰማይና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአንተ ነው፤ አንተ ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክና በሁሉም ላይ ሥልጣን ያለህ ንጉሥ ነህ፤
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።