ኢዮብ 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካስማው እንደ ተነቀለ ድንኳን ያለ ጥበብ ይሞታሉ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ ጥበብ ይሞቱ ዘንድ፣ የድንኳናቸው ገመድ አልተነቀለምን?’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ።’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እፍ ብሎባቸዋልና ይደርቃሉ፥ ጥበብም የላቸውምና ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ። |
የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።
እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።