ኢዮብ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ የማይተማመንባቸው ከሆነ፥ በመላእክቱ እንኳ ስሕተት የሚያገኝባቸው ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት ካልጣለ፣ መላእክቱንም በስሕተታቸው ከወቀሠ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በአገልጋዮቹ እንኳን አይተማመንም፥ በመላእክቱንም ላይ ስሕተት ያገኛል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ አገልጋዮቹንም አይተማመናቸውም፥ መላእክቱንም በጭንቅ ይጠራጠራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፥ መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፥ |
መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤
እንዲሁም ማዕርጋቸውን ባለመጠበቅ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት አስታውሱ፤ እነርሱን እግዚአብሔር እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በዘለዓለም እስራት፥ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጠብቆ አቆይቷቸዋል።