ኢዮብ 4:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ከባድ እንቅልፍ በሚይዛቸውና በሚያስጨንቅ የሌሊት ቅዠት ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊት ሕልም አሳብ ሲነሣ፥ የከበደም እንቅልፍ በሰው ላይ ሲወድቅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰዎች ላይ ፍርሀት በወደቀ ጊዜ በሌሊት ከፍርሀትና ከድምፅ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሊት ሕልም አሳብ ሲነሣ፥ የከበደም እንቅልፍ በሰው ላይ ሲወድቅ፥ |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤
ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤