ኢዮብ 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፥ እንዲህም አለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦ |
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
ከዚህ በኋላ ቴማናዊው ኤሊፋዝ፥ ሹሐዊውም ቢልዳድና ናዕማታዊውም ጾፋር ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ጸሎት ሰማ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ?