ኢዮብ 39:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጎሽ የተባለው የዱር እንስሳ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ይሆናልን? በበረትህስ ውስጥ ሊያድር ይችላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐሽ ሊያገለግልህ ፈቃደኛ ነውን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጎሽ ያገለግልህ ዘንድ ይፈቅዳልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? |
የኤዶም ሕዝብ እንደ ጐሽ፥ እንደ ኰርማና እንደ ወይፈን ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ከሌሎች ጋር አብረው ይሞታሉ፤ ሀገሪቱም በደማቸው ትነከራለች፤ ምድሪቱም በስባቸው ትዳብራለች።
የዮሴፍ ግርማ እንደ ኰርማ አስፈሪ ነው፤ ቀንዶቹም እንደ ጐሽ ቀንዶች ጠንካሮች ናቸው፤ በእነርሱም ሕዝቦችን ይወጋል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ያባርራል፤ የኤፍሬም ዐሥር ሺሆች የምናሴም ሺሆች እንደዚያው ናቸው።”