ኢዮብ 39:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የበረሓ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ አምጣ ስትወልድ አይተህ ታውቃለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዋልያ የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? የምታምጥበትንስ ጊዜ ትመለከታለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን? |
የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
ስለዚህም ሳኦል በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል “የሜዳ ፍየሎች አለት” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ዳዊትን አሳዶ ለመያዝ ሄደ፤