በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኢዮብ 38:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከምድር ውስጥ ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የመፍለቂያ በሮቹን የዘጋ ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣ በር የዘጋበት ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማኅፀን እንደሚወጣ በወጣ ጊዜ ባሕርን በመዝጊያዎች የዘጋ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናቷ ማኅፀን በወጣች ጊዜ፥ ባሕርን በመዝጊያዎች ዘጋኋት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማኅፀን እንደሚወጣ በወጣ ጊዜ ባሕርን በመዝጊያዎች የዘጋ ማን ነው? |
በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥ የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው? ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ በሚዛን የሚመዝን ማን ነው?
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።