ኢዮብ 38:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድርን ምሰሶዎች አጽንቶ የያዘ ኀይል ምንድን ነው? የዓለምንስ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ? የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥ መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር? የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር? የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥ መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር? የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው? |
ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው ጊዜ እንደ አዲስ ተክል የሚያድጉና የሚጠነክሩ ይሁኑ፤ ሴቶች ልጆቻችን ለቤተ መንግሥት ማእዘኖች ውበት እንደሚሰጡ፥ ተቀርጸው ቀጥ እንዳሉ ምሰሶች ይሁኑ።
ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።