ኢዮብ 38:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆችዋ ምግብ አጥተው ሲቅበዘበዙ ወደ እኔም ሲጮኹ ለቁራ ምግብ የሚሰጣት ማነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቿ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ ምግብ ዐጥተው ሲንከራተቱ፣ ለቍራ መብልን የሚሰጥ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቁራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም ፈልገው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው? |
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
እስቲ ቊራዎችን ተመልከቱ! እነርሱ አይዘሩም ወይም አያጭዱም፤ የእህል ማከማቻ ቦታ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች የቱን ያኽል ትበልጣላችሁ!