ኢዮብ 37:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መብረቁን ከሰማይ በታች ሁሉ ያሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ይልካል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ሁሉ በታች ብርሃኑን ይለቅቃል፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ይልካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል። |
ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።
በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።