ኢዮብ 32:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮብ “እኔ ጻድቅ ሰው ነኝ” ብሎ በሐሳቡ ስለጸና፥ ሦስቱ ሰዎች ንግግራቸውን አቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮብ በበኩሉ ራሱን እንደ ጻድቅ ቈጥሮ ስለ ነበር፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለርሱ መልስ መስጠታቸውን ተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮብም በፊታቸው ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ወዳጆቹ ለኢዮብ ለመመለስ ዝም አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ። |