ኢዮብ 30:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከችግርና ከራብ ብዛት የተነሣ፥ ወደ በረሓ እየሄዱ ሥራ ሥሮችን ያኝኩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከችጋርና ከራብ የተነሣ ጠወለጉ፤ ሰው በማይኖርበት በረሓ፣ በደረቅም ምድር በሌሊት ተንከራተቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በችግርና በራብ መንምነው፥ በፈረሰውንና በተተወው የጨለመ ምድረ በዳን ሥራ ሥሮችን ያኝካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትላንት በድካምና በውርደት ከምድረ በዳ ያመለጡ፥ ከረኃብ የተነሣ ተሰድደው ይለምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራብና በቀጠና የመነመኑ ናቸው፥ የመፍረስና የመፈታት ጨለማ ወዳለበት ወደ ምድረ በዳ ይሸሻሉ። |
ከሕዝብ መካከል ተባረረ፤ አእምሮውም ተለውጦ እንደ እንስሳ ሆነ፤ እንደ በሬም ሣር እየበላ ከሜዳ አህዮች ጋር ሆኖ ለመኖር ተገደደ፤ መጠለያ አጥቶ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትን ሁሉ ለፈለገው መስጠት እንደሚችል እስከሚረዳበት ጊዜ ድረስ ነበር።