ኢዮብ 3:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንገዱ ለተሰወረበትና እግዚአብሔር ለዘጋበት ሰው ብርሃን የሚሰጠው ለምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤ እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ ሕይወት ለምን ተሰጠ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለምን ተሰጠ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞት ለሰው ዕረፍቱ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ከለከለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለ ምን ተሰጠ? |
የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! “አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤ መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤” ብለህ ለምን ታማርራለህ?