ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።
ኢዮብ 27:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶቼ እንደ ኃጢአተኞች፥ ተቃዋሚዎቼም እንደ ግፈኞች ይፈረድባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ ባላንጣዬም እንደ ክፉ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጠላቴ እንደ በደለኛ፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶች እንደ ኀጢአተኞች ውድቀት፥ በእኔ ላይም የሚነሡ እንደ በደለኞች ጥፋት ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቴ እንደ በደለኛ፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን። |
ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።
“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!
በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል እጅግ ከመደንገጡና በሐሳብ ከመታወኩ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ፤ ንጉሡም “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ አያስጨንቅህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ ለአንተ መሆኑ ቀርቶ ለጠላቶችህ ቢሆን በወደድሁ ነበር።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤