በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።
ኢዮብ 26:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከውቅያኖስ በታች ያሉት የሙታን ነፍሳት በከባድ መንቀጥቀጥ ላይ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣ የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙታን ከውኆች በታች፥ በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን ከውኆች በታች፥ በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ ይወለዳሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙታን ሰዎች ከውኆች በታች፥ በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ። |
በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።