ኢዮብ 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚገኝበትን ቦታ ባውቅ እንዴት በወደድሁ ነበር፤ ወደሚኖርበትም ቦታ ብደርስ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱን ወዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ነገሩ ፍጻሜም ምነው በደረስሁ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱን ወዴት እንዳገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ! |
ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።
እነዚያ መልካሙን ዜና በመጀመሪያ የሰሙት ባለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው የዕረፍት ቦታ አልገቡም፤ ሆኖም ወደዚያ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አንዳንዶች ነበሩ።