ኢዮብ 22:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር የኀይለኛ ሰዎች ንብረት፥ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ይዞታ ሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለርስትና ኀያል፣ በርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይለኛ ሰው መሬት ገዛ፥ የተከበረ ሰው ተቀመጠባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊታቸውን አይተህ ያደነቅሃቸው አሉ፥ በምድርም ላይ ድሆችን በዐመፅ ጠላህ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክንድ የበረታ ምድርን ገዛ፥ ከበርቴውም ሰው ተቀመጠባት። |
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።