ኢዮብ 22:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተርበውና ተጠምተው ለደከሙ እህልና ውሃ ከልክለሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤ የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥም የደከመውን ውኃ አላጠጣህም፥ የተራበውንም እንጀራ ከልክለሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለተጠማ ውኃ አላጠጣህም፥ የራብተኛውንም ጕርሻ ነጥቀሃል፥ ምድርን የሚዘራ ሰውም በውስጧ ድንበርን ያኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደካማ ውኃ አላጠጣህም፥ ለራብተኛም እንጀራን ከልክለሃል። |
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?