ኢዮብ 22:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በእርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ ንብረታቸውም ሁሉ በእሳት ጋይቶአል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘በርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ ሀብታቸውም በእሳት ተበልቷል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነት ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፥ ከንብረታቸው የተረፈውንም እሳት በላች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነት ሀብታቸው ጠፋ፥ የቀረውንም እሳት በላች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነት ሀብታቸው ጠፋ፥ የቀረውንም እሳት በላች። |
የመጀመሪያው መልእክተኛ ንግግሩን ገና ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጣና “በጎቹንና እረኞቹን በሙሉ መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ገደላቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።
ያካበተው ንብረት ሁሉ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ ይወድማል፤ በሰው እጅ ያልተቀጣጠለ እሳትም ያቃጥለዋል፤ በቤቱ ውስጥ የሚተርፈውን ንብረት ሁሉ ያጋየዋል።