ኢዮብ 21:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስቲ ንግግሬን በጥሞና አድምጡኝ፤ በዚህም እኔን እንዳጽናናችሁኝ ይቈጠርላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቃሌን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም በዚህ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፥ ይህም እንደ ማጽናናት ይቆጠርላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኛ አጽናናነው እንዳትሉኝ፥ ስሙ፤ ቃሌን ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፥ ይህም መጽናናታችሁ ይሁን። |
ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።
ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።