ኢዮብ 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሚኖርበት ቦታ ደብዛው ስለሚጠፋ፥ አንድ ጊዜ የተመለከተው ሰው ዳግመኛ አያየውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየችውም ዐይን ዳግመኛ አታየውም፥ ለስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ ይሰወራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይን አየችው፤ ነገር ግን ዳግመኛ አታየውም፤ ስፍራውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየችውም ዓይን ዳግመኛ አታየውም፥ ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከተውም። |