ኢዮብ 20:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ሕልም ብን ብሎ ስለሚጠፋ አይገኝም፤ እንደ ሌሊት ራእይም ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሕልም ይበርራል፤ እርሱም አይገኝም፤ ሲነጋም እንደማይታወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰደዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል። |
ከቶ ኃጢአቴን ይቅር አትልልኝምን? የማደርገውንስ በደል አትደመስስልኝምን? ወደ መቃብር መውረጃዬ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ብትፈልገኝ እንኳ አልገኝም።”
ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።