ኢዮብ 20:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! የሕሊናዬ ብስጭት መልስ እንድሰጥህ አስገደደኝ፤ ስለዚህም ነው ለመናገር የቸኰልኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እጅግ ታውኬአለሁና፣ ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጕተኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንድመልስ ሐሳቤ ይገፋፋኝል፥ ስለዚህም ውስጤ መታገሥ አቅቶታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደዚህ እንደምትመልስ አልጠረጠርሁህም ነበር፤ በዕውቀትም ከእኔ አትሻልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በውስጤ ስላለው ችኰላ አሳቤ ትመልስልኛለች። |
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።