La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሥቃዩንም ብዛት ስላዩ ምንም ቃል ሳይናገሩ ከእርሱ ጋር ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት በመሬት ላይ ተቀምጠው ሰነበቱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከርሱ ጋራ መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሥቃዩ ታላቅ መሆኑንም ስለ ተረዱ፣ አንዳች ቃል የተናገረው አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተው ነበርና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​መጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስ​ፈ​ሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ አንድ ቃል የሚ​ና​ገ​ረው አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።

Ver Capítulo



ኢዮብ 2:13
12 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ብርሃኑን “ቀን” ብሎ ጠራው፤ ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አንድ ቀን ሆነ።


እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ።


ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


እኔም ይህን በሰማሁ ጊዜ በሐዘን መጐናጸፊያዬንና ካባዬን ቀደድሁ፤ የራስ ጠጒሬንና ጢሜን በመንጨት በብርቱ ሐዘን ላይ ሆኜ ተቀመጥሁ፤


እኔም ይህን ሁሉ በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስኩ። ለብዙ ቀኖችም በጾምና በሐዘን ቈየሁ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ስል ጸለይኩ፦


ከዚህ በኋላ ኢዮብ መናገር ጀመረ፤ የተወለደበትን ቀን እንዲህ ሲል ረገመ፦


“ኢዮብ ሆይ! አንድ ሰው ደፍሮ ቢናገርህ በትዕግሥት ታዳምጣለህን? ነገር ግን ከመናገር ማን ይቈጠባል?


ሌሊቱን ሙሉ አነቃኸኝ፤ ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም።


የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።


የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።


ስለዚህ በኬባር ወንዝ አጠገብ ወዳለው ወደ ቴል አቢብ መጣሁ፤ ይህም ስፍራ የምርኮኞች መኖሪያ ነበር፤ ባየሁትና በሰማሁት ነገር ሁሉ በመደንገጥ ደንዝዤ በመካከላቸው ሰባት ቀን ቈየሁ።