ኢዮብ 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤
በዚህ ጊዜ የኢዮብ ወንድሞች፥ እኅቶችና ቀድሞ የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ሊጐበኙት መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ተመገቡ፥ ሐዘናቸውን በመግለጥ እግዚአብሔር ስላደረሰበት ብርቱ መከራ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም የብርና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት።
እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ።
ከዚህ በኋላ ቴማናዊው ኤሊፋዝ፥ ሹሐዊውም ቢልዳድና ናዕማታዊውም ጾፋር ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ጸሎት ሰማ።
ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ?
አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።
ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደ ታሰራችሁ ያኽል ሆናችሁ እስረኞችን አስታውሱ፤ እናንተም እንደ እነርሱ መከራ የምትቀበሉ ያኽል ሆናችሁ መከራ የሚቀበሉትን አስቡ።
ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።