ኢዮብ 19:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ዐሥር ጊዜ ትሰድቡኛላችሁ፤ ስታዋርዱኝም አታፍሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸው ስትሰድቡኝ ዐሥር ጊዜ ነው፥ ስታሰቃዩኝም አላፈራችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር ጊዜ ትናገሩኛላችሁ፥ ትሰድቡኛላችሁም፤ በሰውነቴ ላይ በጠላትነት ስትነሡብኝ አታፍሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸው ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፥ ስታሻክሩኝም አላፈራችሁም። |
ዮሴፍ ወንድሞቹን ባያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቊጣ ቃል “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እህል ለመሸመት ከከነዓን አገር መጣን” አሉት።
ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው።
ምግብ እንድታጡ በማደርግበት ጊዜ እንጀራችሁን ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፤ ምግባችሁንም መጥነው ያቀርቡላችኋል፤ እናንተም በልታችሁ አትጠግቡም።
ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።