ኢዮብ 19:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስከ መቼ ድረስ ታሠቃዩኛላችሁ? እስከ መቼስ በነገር ቅስሜን ትሰብሩታላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነፍሴን የምታስጨንቋት፣ በቃልስ የምትደቍሱኝ እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነፍሴን የምትነዘንዙት፥ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነፍሴን የምትነዘንዙአት፥ በቃላችሁስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገብኝ ዕወቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴን የምትነዘንዙ፥ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? |
ንግግሩ እንደ ቅቤ የለዘበ ነው፤ በልቡ የሚያስበው ግን ጦርነትን ነበር አንደበቱ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው፤ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ነው።
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።