ኢዮብ 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኞች በዚህ ነገር ተደናግጠዋል፤ ንጹሖች እግዚአብሔርን በማያምኑ ሰዎች ላይ ተቈጥተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይረበሻሉ፥ ንጹሕም አምላኩን በሚክድ ላይ ይበሳጫል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስታዬን ተማምኛት ነበር፤ ነገር ግን ጠፋችብኝ፤ አግባብስ ወደ ኃጥኣን ትመለስ ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሕም በዝንጉው ላይ ይበሳጫል። |
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
ጳውሎስና በርናባስ ግን እንዲህ ሲሉ በድፍረት ተናገሩ፤ “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ እንዲነገር አስፈላጊ ነው፤ እናንተ አንቀበልም ካላችሁና የዘለዓለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን እነሆ፥ እኛ ዞር ብለን ወደ አሕዛብ እንሄዳለን።