ኢዮብ 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሰዎች መዘባበቻ አደረገኝ፤ ሰዎቹም በፊቱ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላክ ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሕዛብም ምሳሌ አደረግኸኝ፤ መሳቂያና መዘባበቻም ሆንኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ። |
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ላይ ቢተፋባት እንኳ ኀፍረትዋን ተሸክማ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ትቈይ የለምን? ስለዚህም እርስዋ ከሰፈር ወጥታ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በገለልተኛ ቦታ ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሳ ወደ ሰፈር ልትገባ ትችላለች።”