ኢዮብ 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁላችሁም እንደገና መጥታችሁ በፊቴ ብትከራከሩ ከመካከላችሁ አንድ እንኳ አስተዋይ ሰው አላገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስኪ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ! ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥ በእናንተም ዘንድ ጠቢብ አላገኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ወደዚህ መጥታችሁ ታዩኛላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ እውነትን አላገኘሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥ በእናንተም ዘንድ ብልሃተኛ አላገኝም። |
እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ።