ኢዮብ 15:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚፈርድብህ የገዛ አንደበትህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ አነጋገርህም ያጋልጥሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚፈርድብህ አንደበትህ እንጂ እኔ አይደለሁም፣ የሚመሰክርብህም እኔ ሳልሆን የገዛ ከንፈርህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል። |
እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል። በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ።
በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው በብስጭት ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሮአል! እናንተም ስድቡን ሰምታችኋል! ከዚህ የበለጠ ምን ምስክር ያስፈልጋል!
ጌታውም ‘አንተ መጥፎ አገልጋይ! በአነጋገርህ እፈርድብሃለሁ፤ እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የምሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆኔን ዐውቀሃል፤