ይልቅስ ዝም ብትሉ ኖሮ ጠቢባን መስላችሁ በታያችሁ ነበር!
ምነው ዝም ብትሉ! ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር።
ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር።
ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥ ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና።
ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን? ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን?
እስቲ ዝም በሉ እኔም እንድናገር ዕድል ስጡኝ ከዚያ በኋላ የፈለገው ነገር ይሁን።
“የማቀርበውን ክርክር ስሙ፤ በደሌንም ስዘረዝር በጸጥታ አድምጡ።
ይህ ከንቱ ንግግራችሁ መጨረሻ የለውምን? ከእኔ ጋር ይህን ያኽል ለመከራከር ያነሣሣችሁ ምክንያት ምንድን ነው?
“ኢዮብ ሆይ! ለምን እንደዚህ ንግግር ታበዛለህ? እስቲ አድምጥ፤ እኛም እንናገር።
“እስከ መቼ ድረስ ታሠቃዩኛላችሁ? እስከ መቼስ በነገር ቅስሜን ትሰብሩታላችሁ?
እስቲ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ መናገር እስኪያቅታችሁ ድረስ ሁኔታዬ ያሠቅቃችኋል።
ኢዮብ “እኔ ጻድቅ ሰው ነኝ” ብሎ በሐሳቡ ስለጸና፥ ሦስቱ ሰዎች ንግግራቸውን አቆሙ።
እነሆ! እነርሱ የሚናገሩትን አጥተው ዝም ብለው ቆመዋል፤ ታዲያ፥ እነርሱ ጸጥ ቢሉ፥ እኔም በትዕግሥት መጠባበቅ ይገባኛልን?
ሞኝ ዝም ሲል ጥበበኛ ይመስላል፤ ምንም ሳይናገር ቢቀር እንደ ብልኅ ይቈጠራል።
ስለ አንድ ነገር ብታስብ ስለ እርሱ ታልማለህ፤ ብዙ ከመናገር የተነሣ ትሳሳታለህ፤
ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ስለ ሆነ አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርና ለቊጣም የዘገየ ይሁን።