ኢዮብ 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሳሌያዊ አነጋገራችሁ እንደ ዐመድ ዋጋ ቢሶች ናቸው፤ ክርክራችሁም እንደ ሸክላ ተሰባብሮ ይወድቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣ መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስሌዎቻችሁ የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፥ ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሳሌያችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤ ሥጋችሁም እንደ ትቢያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስሌዎቻችሁ የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፥ ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።