ኢዮብ 13:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቶታል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውሎታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አየች፥ ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አየች፤ ጆሮየም ሰማች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አየች፥ ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለችው። |
“ድል አድራጊውን አነሣሥቶ ከምሥራቅ ያመጣ፥ እንዲያገለግለው የጠራው ማነው? ሕዝቦችን አሳልፎ ለእርሱ ይሰጣቸዋል። ነገሥታትንም ያስገዛለታል፤ በሰይፉ እንደ ትቢያ በፍላጻዎቹም እንደ ገለባ ይበታትናቸዋል።
ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን። አንድነታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።